የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ ክስ "ተቀባይነት የለውም" አለ
Your browser doesn’t support HTML5
መኢአድና ሰማያዊ አቅደውት የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ያልተካሄደው፣ በራሳቸው በፓርቲዎቹ ምክንያት እንደሆነ የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ስብሰባውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ የተለመዱ ሂደቶችን ተከታትለው፣ አላጠናቀቁም ነው ያለው፡፡