ኮሚሽኑ የምርመራ ቢሮ በኢትዮጵያ ሊከፍት እንደሚችል በውይይት ላይ የተሳተፉ ገለፁ
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ መንግሥት ይፈፀማሉ የሚባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለማጣራትና ለመፈተሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽን በኢትዮጵያ የምርመራ ቢሮ ሊከፍት እንደሚችል ከእስር ከተፈቱት ጋራ በነበራቸው ውይይት መነሳቱን ከተወያዮቹ መካከል ጥቂቶቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውን አሕመዲን ጀበልና የኢንተርኔት አምደኛው በፍቃዱ ኃይሉ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።