በድሬደዋው ግጭት አራት ሰው ቆስሏል ተብሏል
Your browser doesn’t support HTML5
በድሬዳዋ ከተማ በጥምቀት አከባበር በዓል ላይ ያልታወቁ ሰዎች በምዕመናን ላይ የፈፀሙትን ትንኮሳ ተከትሎ የተነሳው አለመረጋጋት ዛሬ ተባብሶ ቀጥሏል። ተቃውሞውም ሃይማኖትን ከመከላከል ወደ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተሻግሯል። በከተማው የታሰሩ ወጣቶች እንዲፈቱም ተጠይቋል። በዛሬው ዕለት በአብዛኞቹ የከተማዋ መንገዶች፣ የንግድ ማዕከላት የሆኑት ቀፊራ፣ ኮኔል፣ ታይዋን፣ ሩዝ ተራ፣ አሸዋና አካበቢው ያሉ መደብሮችና ባንኮችም ተዘግተው ውለዋል፡፡