የኢትዮጵያ መንግስት ደሴና ኮምቦልቻን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር

የአማጺው የትግራይ ኋይሎች ተቆጣጥረዋቸው የነበሩትና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ተንታኞች "ቁልፍ" ስፍራ ናቸው የተባሉት ደሴና ኮምቦልቻን የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃ ማውጣቱን ማምሻውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል የሚገኙት ደሴ እና ኮምቦልቻን እንዲሁም ባቲን ጨምሮ በምስራቅ ግንባር የሚገኙ በርካታ ከተሞች በኢትዮጵያ በመንግስት የጸጥታ ኋይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግስት ደሴና ኮምቦልቻን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

ከጥቅምት ወር ጀምሮ በአማጽያኑ የትግራይ ኋይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩትና በዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት እና ተንታኞች ለጦር አሰላለፍ ቁልፍ መሆናቸው ሲነገር የቆየው ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በተመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

ታሪካዊ ከተማ ከሆነችው ደሴ እና በንግድ እና ኢንዱስትሪ ኮሪደርነቷ ከምትታወቀው ኮምቦልቻ በተጨማሪም የኢዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው እንዲሁም እራሳቸውን የትግራይ ሰራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የምትገኘው የባቲ ከተማ ፣ቀርሳ፣ ገርባና ደርጋን ከተሞችን የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ ማውጣቱን የኮሚዩኒኬሽን ቢሮው ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ በሐርቡ ግንባር ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል።

ከዛሬ በፊት በነበሩት ቀናት ታሪካዊቷን የላሊበላ ከተማ እና ጋሸናን ነፃ ማውጣቱን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾ የነበረሲሆን በነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንአስታውቋል። በተጨማሪም በላሊበላ የውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እስካሁን በውልአለመታወቁን ሆኖም ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ለታሪካዊ ቅርሱ አስፈላጊውን ጥገና ለማድረግ ጋር ዝግጅትመጀመሩን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ይህን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግስት አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር የማህበራዊ ትስስር ገፃቸውባሰፈሩት መልዕክት የትግራይ አማፂያን ቡድኑ ይዟቸው በነበሩ ግዛቶች ላይ ማስተካከያ እያደረገ መሆኑንና ቀጣዩርምጃቸው ስልታዊ ክንዋኔዎችን ያገናዘበ እንደሆነ አስታውቀዋል። የውሳኔያቸው አላማ በዋናነት የህዝባቸውን ደህነትማስጠበቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጌታቸው በመጪው ሳምንታት ውጤት የሚያስገኝላቸው ሁኔታ ላይ እንደሚደርሱተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ጨምረው ከጣርማ በር እስከ ደሴ ባሉ ውጊያዎች ጠላትን ማሸነፋቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው በጥቅምት ወር ከተሞቹን መቆጣጠራቸውን ለሮይተርስ በተናገሩበት ወቅት አማጺያኑ ከፌደራል መንግስቱጋር እያደረጉት ባለው ውጊያና ወደ አዲስ አበባ በሚያደርጉት ግስጋሴ ስልታዊ ድል መሆኑ ተገልጾ ነበር።