ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ጦርነት “እጅግ አሰቃቂ” ጥቃት እንደደረሰባቸው ገለፁ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በእጅጉ ተረብሸው እና የሚያደርጉት ጠፍቷቸው፤ ከሚወዷቸው የቤተሰብ አባላት ተነጣጥለው፣ ከቦምብ እና ከተኩስ ለማምለጥ መሸሸጊያ ፍለጋ እግራቸው ወዳመራቸው ሲጓዙ ማየት በኢትዮጵያ ለተራዘመ ጊዜ በተካሄደው ጦርነት የተለመደ ትእይንት እየሆነ መጣቷል።በምስራቅ አፋር ክልል በሚገኘው የባህራሌ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከደረሰው ጥቃቱ የተረፉ ወገኖች ከአጎራባች ትግራይ በመጡ ተዋጊዎች ተፈፅሞብናል ያሉት ጥቃት “እጅግ አሰቃቂ” ሲሉ ጠርተውታል።