ጅቡቲ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ጅቡቲ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ በአሊ አዴህ መጠለያ ጣቢያ ከ8 እስከ 14 ዓመታት እንደኖሩ የሚናገሩት ስደተኞቹ፣ የምግብና የሕክምና እጥረት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር / ዩኤን ኤች ሲ አር/ በበኩሉ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ፣ ለጅቡቲ ስደተኞች ሲሰጥ ነበረው የምግብ እርዳታ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በገንዘብ እጥረት ምክኒያት በግማሽ መቀነሱን ገልፆ በዚህ ዓመት ግን መስተካከሉን አስታውቋል፡፡