ካማሺ ውስጥ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ከክልሉ መንግሥት ጋራ የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ወደ መደበኛ ኑሯቸው ከገቡ ወዲህ ሰላም መስፈኑን የካማሺ ከተማ አንዳንድ ነዋሪዎች ገለጹ። የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቦዴፓ/ በክልሉ ሳይካሄድ የቀረው የሰኔ 2013 አጠቃላይ ምርጫ እንዲካሄድም አሳስቧል። ሆኖም በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ጽሕፈት ቤት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች በቅርቡ ምርጫ ለማካሄድ የተያዘ መረኃ-ግብር እንደሌለ አስታውቋል።