ኬኒያ የወጣቶችን እርግዝና ለመቀነስ የወሲብ ማስተማሪያ መተግበሪያ ጀመረች
Your browser doesn’t support HTML5
ኬንያ የታዳጊዎች እርግዝና ችግር ለመቅረፍ በዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥ የወሲብ ትምህርት መጀመሩ ከ5ሺህ በላይ ወጣቶችን መሳብ እንደቻለ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። በስዋሂሊ ቋንቋ 'ኔና ና ቢንቲ' ወይም 'ከአንድ እህት ጋር ተነጋገሩ' የተሰኘው አገልግሎት በሞባይል መተግበሪያ እና ከክፍያ ነፃ በሆነ የስልክ ጥሪ አማካኝነት፣ በእርግዝና መጠን በዓለም ሦስተኛ ከፍተኛ ደረጃ ለያዙት የኬንያ ታዳጊዎች፣ በስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ መረጃ እና የምክር አገልግሎት ይሰጣል።