በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂ ስኬታማ ያደረገው ተቋም
Your browser doesn’t support HTML5
በዓለም ዙሪያ ተፈላጊ ከሆኑ ስራዎች በግምባር ቀደምነት በሚጠቀሰው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በብቃት ከሚያሰለጥኑ ተቋማት መካከል አንዱ በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ግዛት የሚገኘው ቤማንዳ ቴክኖሎጂ ነው። ቤማንዳ እስካሁን ከ1ሺህ ሦስት መቶ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ስራ ያስያዘ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ቅርጫፍ በመክፈት የስልጠናና እና የማማከር አገልግሎቱን እያሰፋ እንደሚገኝ የተቋሙ መስራች አቶ አለማየሁ ኒዳ ነግረውናል።