የምስራቅ ወለጋ አኖ ከተማ ነዋሪዎች ሰለ ሠላም ይናገራሉ

በኦሮምያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ አኖ ከተማ ባለፈው ሳምንት ጥር 25/2015 ዓ.ም በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለው ጥቃት 60 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የዐይን እማኞችና የተጎጂ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በከተማው ውስጥ ውጥረት መንገሱንና ነዋሪዎች ሥጋት ውስጥ መግባታቸውን ወደ ስፍራው አቅንቶ የነበረው የአምቦው ዘጋቢያችን ከስፍራው ያጠናቀረውን ማሰማታችን ይታወሳል።

Your browser doesn’t support HTML5

የምስራቅ ወለጋ አኖ ከተማ ነዋሪዎች ሰለ ሠላም ይናገራሉ

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ታጣቂዎች በሚፈጽሙት ጥቃት እና በነዋሪው ህዝብ ደህንነት ላይ በቀኑት ስጋት ሳቢያ የነበራቸው ማኅበራዊ መስተጋብር መላላቱን፣ የኑሮ ሁኔታ መክበዱንና ወጥቶ መግባትም ሥጋት መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

የፀጥታ ችግር የደቀነውን ፈተና እና በአካባቢው ሰላም ይሰፍን ዘንድ መደረግ አለበት የሚሉትን ጨምሮ ናኮር የከተማይቱ ነዋሪ ከሆኑ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ጋር ያደረገውን ውይይት ይዞ ቀርቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።