የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጨማሪ ትኩረት ይፈልጋል
Your browser doesn’t support HTML5
የማህፀን ጫፍ ካንሰር በቀላሉ መከላከል እና ቀደም ብሎ ከታወቀ ሊድን የሚችል የካንሰር አይነት ቢሆንም በአፍሪካ በየዓመቱ ከ70 ሺህ በላይ ሴቶች በዚህ ካንሰር ህይወታቸው ያጣሉ። በኢትዮጵያም በየዓመቱ ከ7ሺህ በላይ ሴቶች በዚህ ካንሰር እንደሚያዙ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር መረጃ ያመለክታል። ለመሆኑ የማህፀን ጫፍ ካንሰር በምን ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው? በቀላሉ መከላከል እና ማዳን ከተቻለስ ለምን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉ?