የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጨማሪ ትኩረት ይፈልጋል

Your browser doesn’t support HTML5

የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጨማሪ ትኩረት ይፈልጋል

የማህፀን ጫፍ ካንሰር በቀላሉ መከላከል እና ቀደም ብሎ ከታወቀ ሊድን የሚችል የካንሰር አይነት ቢሆንም በአፍሪካ በየዓመቱ ከ70 ሺህ በላይ ሴቶች በዚህ ካንሰር ህይወታቸውን ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥም በየዓመቱ ከ7ሺህ በላይ ሴቶች በዚህ ካንሰር እንደሚያዙ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ያመለክታል። ከነዚህ ውስጥ 5 ሺህ 338 የሚሆኑትም ህይወታቸውን እንደሚያጡ ገልጿል። ለመሆኑ የማህፀን ጫፍ ካንሰር በምን ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው? በቀላሉ መከላከል እና ማዳን ከተቻለስ ለምን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉ ስትል ስመኝሽ የቆየ የተለያዩ ሴቶችን እና የካንሰር ህክምና ባለሙያዎችን አነጋግራለች።