ስኬታማ ልጆችን የማሳደግ ሚስጥር
Your browser doesn’t support HTML5
ወላጆች ልጆችን በማሳደግ ሂደት ውስጥ የሚጠብቃቸውን ኃላፊነት እንዲያውቁ እና ለእያንዳንዱ የልጆቻቸው የዕድገት ደረጃ እንዲዘጋጁ የሚረዳ ስልጠና አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዷል። ኦአሲስ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተቋም፣ 'ፓሬንቶን' በሚል ስያሜ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ዋና ዓላማው፣ ዕድሜ ልክ በሚዘልቀው ልጅን የማሳደግ ሂደት ውስጥ ሁለንተናዊ የልጆች አስተዳደግ ምን እንደሚመስል ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን፣ ወላጆች ለማህበረሰብ ግንባታ ያላቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።