የአብን አባል አቶ ጣሂር ሙሃመድ በሌላ ሰው ተተኩ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ አባል አቶ ጣሂር መሐመድ፣ ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነታቸው ተነስተው፣ በሌላ የአብን አባል መተካታቸውን ክልሉ አስታወቀ።

አቶ ጣሂር ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ቢያረጋግጡም፣ ክልሉ ግን ሥራ ላይ ባለመገኘት እና በሀብት ብክነት ወቅሶ እንዳነሳቸው ገልጿል።

አቶ ጣሂር ክልሉ ባሰማው ክስ እና ወቀሳ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን፣ደጋግመን ብንሞክርም ሊሳካልን አልቻለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።