ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው ሀገራት ብድሮቻቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

በቅርቡ፣ በናይሮቢ ኬኒያ በተካሔደው የአፍሪካ ልማት ባንክ የ2024 ዓ.ም. ጉባኤ ላይ የተገኙት፣ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ አፍሪካውያን በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ላይ እንዲያተኩሩ ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ደግሞ፣ የሚገኘው ብድር በአግባቡ ለልማት መዋል እስካልቻለ ድረስ፣ በአጭር ጊዜም ይወሰድ በረጅም ጊዜ የሚያመጣው ለውጥ አለመኖሩን ይናገራሉ።