በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንበሰሀላ ሰየምት ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች በተከሠተው አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት፣ ባለፈው ሳምንት ብቻ አምስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 262ቱ ደግሞ በጽኑ መታመማቸውን፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ገልጸዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
በሰሀላ ሰየምት ወረዳ በአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ሕመም አምስት ሰዎች መሞታቸውን ዞኑ አስታወቀ
ለተጨማሪ ምርመራ፣ ናሙና ወደ ክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላክ በዝግጅት ላይ መኾኑን የጠቆሙት ኃላፊው፣ የሕመሙን መስፋፋት ለመቆጣጠር ድጋፍ ሰጭ የሐኪሞች ቡድን ወደ ስፍራው ተልኮ የመከላከል ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በወረዳው የቢላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ በበኩላቸው፣ በቀበሌው አራት ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎች ታመው መተኛታቸውን አመልክተዋል።