ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ችግሩን እንዴት መፍታት ይቻላል? በሚለው ላይ ለመወያየት ስመኝሽ የቆየ በአሜሪካ የመድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደር መስሪያ ቤት ውስጥ በፔዲያትሪክ ፋርማኮሎጂስትነት የምታገለግለውን ዶክተር ሊሊ ሙሉጌታ እና የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያ እና በአፍሪካ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ኮሌጅ ተደራሽነት ዙሪያ የሚሰራ ተቋም መስራች ማቲዮስ መስፍንን ስቱዲዮ ጋብዛ አነጋግራለች።
ራሳቸውን የሚያጠፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ቁጥር ለምን ጨመረ?
Your browser doesn’t support HTML5
አሜሪካ ውስጥ በየ11 ደቂቃው አንድ ሰው ራሱን እንደሚያጠፋ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መስሪያቤት መረጃ ያሳያል። ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ አሜሪካውያን ራሳቸውን አጥፍተዋል። በተለይ እድሜያቸው ከ10 - 24 ዓመት ባሉ ወጣቶች ዘንድ ዋና የሞት መንስዔ መሆኑንም ተመልክቷል። ይህ ቁጥር ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣቶችንም ያጠቃልላል። ቁጥሩ በጥናት ባይረጋገጥም፣ ራሳቸውን የሚያጠፉ ኢትዮጵያዊ አሜሪካውያን ወጣቶች ቁጥር እየጨምረ መሄዱን ባለሙያዎች ይናገራሉ።