Your browser doesn’t support HTML5
በትግራይ ክልል በፍጥነት እየተዛመተ ነው በተባለ የኮሌራ በሽታ ሰባት ሰዎች ሞቱ
በትግራይ ክልል በአንድ ወር ውስጥ በኮሌራ በሽታ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በጤና ቢሮው የኅብረተሰብ ጤና ክብካቤ አስተባባሪ አቶ መብራህቶም ሀፍተ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ በሽታው በክልሉ በፍጥነት እየተዛመተ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በ25 ወረዳዎች መታየቱን ተናግረዋል፡፡
የበሽታውን መዛመት ለመግታት ጥረት እያደረገ መኾኑን ጤና ቢሮው ገልጾ፣ ኹኔታው ግን ከዓቅም በላይ እየኾነ በመምጣቱ፣ ክልሉ የፌደራሉን መንግሥት እገዛ መጠየቁንም አስተባባሪው አመልክተዋል፡፡