ኢራን ትናንት ከ180 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ካስወነጨፈች በኋላ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።
Your browser doesn’t support HTML5
ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤል ማስወንጨፏ ቀጣናውን ወደ ባሰ ትርምስ ይከተዋል - የዲፕሎማሲና አለም አቀፍ ግኑኝነት ተመራማሪ
በውጭ ጉዳይ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ዳር እስከዳር ታየ ኢራን በዋና አጋሯ ሂዝቦላ ላይ እስራኤል የወሰደችው ከባድ ወታደራዊ ርምጃ ሚሳኤል ለማስወንጨፏ ዋና ምክንያት ነው ይላሉ::
ይህ የቀጣናው ትርምስ ወደ ተባባሰ ሁኔታ ለመግባቱ መጀመርያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው ያሉት ዶክተር ዳር እስከዳር እስራኤል ለጥቃቱ የምትሰጠው ምላሽም ቀጣይ ሁኔታውን የሚወስን ይሆናል ብለዋል::