መረጃን በማጣራት ሀሰተኛ መረጃን ለማጥፋት የሚጥረው ወጣት
Your browser doesn’t support HTML5
ከአራት አመት በፊት በሚዲያ ተቋም ይሰሩ በነበሩ ጋዜጠኞች የተመሰረተው ሀቅ ቼክ በኢትዮጵያ ሆን ተብለው ሆነ ባለማወቅ የሚሰራጩ መረጃዎችን በማጣራት የሀሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት ለመቀነስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ ተቋም የመረጃ አጣሪዎች አስተባባሪ ሆኖ የሚያገለግለው ኪሩቤል ተስፋዬም የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘበትን የምህንድስና ሙያ በመተው ሀሰተኛ መረጃ በማህበረሰቡ ውስጥ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።