ሜታ መረጃ የማጣራት ስራ ማቋረጡ ስጋት ፈጥሯል

Your browser doesn’t support HTML5

ሜታ በማህበራዊ የትስስር ገጾቹ ላይ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ ከሶስተኛ ወገን ተቋማት ጋር በመተባበር ያካሂድ የነበረውን የመረጃ ማጣራት ስራ ማቋረጡ ሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እንዲሰራጭ ያደርጋል ሲሉ ተቺዎች ተናግረውል። በአሁኑ ወቅት ውሳኔው በአሜሪካ ውስጥ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለቪኦኤ የገለጸው ፌስቡክ በበኩሉ፣ ከአሜሪካ ውጪ ወዳሉ ሀገራት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ተቋሙ የሚኖሩበትን ግዴታዎች በጥንቃቄ እንደሚያጠና ገልጿል።