Your browser doesn’t support HTML5
የአቶ ታዬ ደንደአ የዋስ መብት ጥያቄ ዳግም ለሳምንት ተቀጠረ
የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የጠየቁት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ችሎቱ ለሁለተኛ ጊዜ የሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዐቃቤ ሕግ ካቀረበባቸው ሦስት ክሶች ሁለቱ ውድቅ የተደረገላቸው አቶ ታዬ፣ እንዲከላከሉ በተበየነባቸው ማለትም “ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በመያዝ” በሚለው ሦስተኛው ክስ ላይ የዋስ መብት አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡