በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ድንበሮች አካባቢ ከአንድ ሣምንት በላይ መዝለቁ የተነገረ ግጭት መርገቡንና መረጋጋት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ድሬዳዋ —
ይሁን እንጂ በማንኛውም ሰዓት ሊያገረሽ እንደሚችል ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ናቸው። እስከአሁን በነበረው ግጭት የአምስት ሰው ሕይወት መጥፋቱና 15 ሰው መቁሰሉ ተሰምቷል።
በሁለቱም ወገኖች የሚታየው እልህ እና ሦስቱን አወዛጋቢ ቀበሌዎች የሚታየው አንዱ ለሌላኛው ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያለመሆን አዝማሚያ ለቀጣይ ግጭቶች መንስዔ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ ታዛቢዎች ሥጋታቸውን እየገለፁ ነው።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ድንበሮች ተከስቶ የነበረው ግጭት