ለሴት ልጆች የተሻለ ህይወት እንትጋ

Your browser doesn’t support HTML5

የዘንድሮው ዓመታዊ የአለም አቀፍ የስነህዝብ ጥናት ዘገባ በጆርዳን ዋና ከተማ በአማን ተካሂዶ ነበር። ዘገባው የአስር አመት ዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ አዳጊ ሴቶችን የወደፊት የህይወት እጣ ለመመርመር ሞክሯል። እንደዘገባው አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን መሰረታዊ ትምህርትና ህክምና ባልተሟላበት፤ ደህንነታቸውም አስጊ በሆነበት ቦታ ነው የሚያድጉት። የፆታ እኩልነትነት አመለካከትብ ለመቀየር የበለጠ መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።