አልሻባብ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ባደረሰው ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

አልሻባብ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ባደረሰው ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ

ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር በምትዋሰን አንድ የሶማሊያ ከተማ ላይ ዛሬ የአልሻባብ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ20 በላይ መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞች ተናገሩ።

በሌላ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የአልሸባብ የሽብር ቡድን መደምሰሱን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለአገር ውስጥ መገናኛ ህዝብ ተናግረዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/