በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ጉባዔ ተካሄደ።
ድሬዳዋ —
የሰላም ጉባዔው በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተቋረጠውን ትምህርት በጥሩ መንፈስ የማስጀመር ዓላማ ያለው ነው ተብሏል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2 ተማሪዎችን ሞት ተከትሎ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ሃሙስና አርብ ተማሪዎችን ዳግም መዝግቧል፣ በትላንትናው ዕለትም በይፋ ዳግም ትምህርት መጀመሩን አስታውቆ ነበር።
በተያያዘ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ከሃላፊነት መነሳታቸውም ተገልጿል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ጉባዔ