የትራምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን ሊመስል ይችላል?

Your browser doesn’t support HTML5

የትራምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን ሊመስል ይችላል?

ተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልፍ ትራምፕ ከቀናት በሁላ ቃለ መሃላ ፈጽመው ስራቸውን ይጀምራሉ::

ቅድሚያ ትኩረት ይሰጡታል ተብሎ በሚጠበቀው ኢኮኖሚ ዙርያ የታክስ ቅነሳን ጨምሮ የኩባንያዎችን ምርታማነት የሚያሳድጉ ማሻሽያዎችን ያደረጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናግረዋል:: ነገር ግን እንደ መጀመርያው የስልጣን ዘመናቸው የግብር ጭማሪን በተመለከተ ከሃገራት ጋር ውዝግብ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ኑሮ ውድነትን ሊያባብስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ::

ከአፍሪካ ጋር በሚደረጉ የንግድ ትብብሮች ከአህጉራዊ ግኑኝነት ይልቅ ከሀገራት ጋር የተናጥል ግኑኝነቶች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚችሉም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡