በምሥራቅ ሃረርጌ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰው ህይወት አለፈ

በምሥራቅ ሃረርጌ የመኪና አደጋ ተከሰተ

በምሥራቅ ሃረርጌ ዞን ጎሮጉቱ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ 10 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የምሥራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋውን ተከትሎ ለ4 ስዓት ምሥራቅ ኢትዮጵያን ከመሀል አገር የሚያገናኘው አገር አቋራጭ መስመር ተዘግቶ እንደነበር ተጓዦች ለቪኦኤ አስታውቀዋል። ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በተደረገ ምክክር መንገዱ መከፈቱንና አደጋ አድራሹንም ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በምሥራቅ ሃረርጌ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰው ህይወት አለፈ