በምስራቅ ሃረርጌ የተለያዩ ወረዳዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ተፈናቅለው የነበሩ አብዛኞቹ ነዋሪዎች ወደቀድሞ መኖሪያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ዞኑ አስታወቀ።
ድሬደዋ —
የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ቦንሲቱ ኢብራሂም እንደገለፁት በዞኑ ካሉት ከ178ሺ በላይ ተፈናቃዮች 100 ሺሕ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የባቢሌ ወረዳ ከ59ሺ በላይ ተፈናቃዮችን ወደቀድሞ መኖሪያቸው መመለሱንም አስታወቀዋል።
ጭናቅሰንና ጃርሶ ወረዳዎች ላይ አሁንም ብዙ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ፤ በጃርሶ፣ ኦሮሞና ገሪ ሶማሌ ጎሳዎች መካከል እርቅ የተካሄደው በቅርቡ በመሆኑ ከእዚያ አካባቢ ተፈናቅለው የነበሩትን ወደፊት ለመመለስ እቅድ መያዙን አስታውቀዋል። ወደቀአቸው የሚመለሱ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ከሁለቱ ወረዳዎች ባሻገር ሌሎች ወረዳዎችም በቅርቡ ሊመልሷቸው የተዘጋጁ ሌሎች ተፈናቃዮች መኖራቸውንም ወይዘሮ ቦንሲቱ አስታውቀዋል፡፡
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
የምስራቅ ሃረርጌ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው