የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን
አድማ የተመቱት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ካሉት የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ግማሹ ቢሆኑም የሃገሪቱ አየር እንዳይዘጋ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን የባለሥልጣኑ ዳይሬክተር ጄነራል ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ባለሙያዎቹ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ የሚሰጥ የጥናት ውጤት በመጭው ሣምንት ለመንግሥት እንደሚቀርብ ዳይሬክተሩ ቢያስታውቁም ሠራተኞቹ የጠየቁትን “የአንድ ሺህ ከመቶ የደመወዝ ጭማሪ ለማሟላት እንደማይቻል” አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጄነራል ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የአየር ትራፊክ ተቆጣጠሪዎች አድማ