አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት እና ምሥራቅ አፍሪካን በሚመለከት የቀደሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ፖሊሲዎች ይዘው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ቃለ መሃላ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛሬ ቃለ መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ብሩህ መጭ ጊዜ የሚጠብቃት መሆኑንና ድሕነት ሊሸነፍ የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሷን አመልክተዋል፡፡
ኃይለማርያም ደሣለኝ ከሃያ ዓመታት በዘለቀ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ነው፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ በአንድ ወቅት፤ ምናልባትም የሁለት ዓመት ተኩል በፊት ይሆናል፤ ቀድሞ ያዲሳባ ዘጋቢያችን፣ የዛሬ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን ጋር ተከታታይ ቃለ-ምልልስ አድርገው ነበር፡፡
ያኔ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቃልአቀባይነታቸው ነበር ከፒተር ጋር የተወየዩት፡፡ በዚያ ውይይታቸው ያተኮሩት ኢሕአደግ ስለሚመራበት የአንድ ፓርቲ የበላይነት ፍልስፍና ሆኖ በዛሬው አዲሱ ሥልጣናቸው ስለሚያራምዱትም ፖሊሲ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
የእስክንድር ፍሬውንና የፒተር ሃይንላይንን ዘገባዎች ያዳምጡ፡፡