የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡
ሄግ-አዲሳባ-ናይሮቢ-ኻርቱም-ዋሺንግተን —
የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡
ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ላይ በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክሥ መሥርቶ ጉዳያቸው ጄኔቫ ላይ እየታየ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ ኬንያታ ደግሞ የፊታችን ኅዳር እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት በመጭው ወር ውስጥ በዚሁ የኬንያ ባለሥልጣናት ክሥና የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ልዩ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የኅብረቱ ሥራ አስፈፃሚ አካል ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኬንያዊው ኤራስቱስ ሞኤንቻ ለፈረንሣዩ የዜና ወኪል ገልፀዋል፡፡
ጉዳያቸው በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በተያዘው ከፍተኞቹ የኬንያ ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ኬንያዊያን የተለያየ አስተያየት አላቸው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሁሴን አል በሽርን የመግቢያ ቪዛ ጥያቄ እያጠናች መሆኗን ገልፃለች፡፡
ለዝርዝር ዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ዓለምአቀፍ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ
Your browser doesn’t support HTML5
አፍሪካዊያን ከአይሲሲ በደቦ ወሙጣታቸውን ኢትዮጵያ ትደግፋለች
የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡
ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ላይ በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክሥ መሥርቶ ጉዳያቸው ጄኔቫ ላይ እየታየ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ ኬንያታ ደግሞ የፊታችን ኅዳር እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት
የአፍሪካ ኅብረት በመጭው ወር ውስጥ በዚሁ የኬንያ ባለሥልጣናት ክሥና የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ልዩ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የኅብረቱ ሥራ አስፈፃሚ አካል ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኬንያዊው ኤራስቱስ ሞኤንቻ ለፈረንሣዩ የዜና ወኪል ገልፀዋል፡፡
ጉዳያቸው በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በተያዘው ከፍተኞቹ የኬንያ ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ኬንያዊያን የተለያየ አስተያየት አላቸው፡፡
በአይሲሲ እየታደኑ ያሉት ኦማር ሁሴን አል-በሽር - የሱዳን ፕሬዚዳንት