የኑሮ ደረጃቸው እንዲሻሻል ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ትዕግስት ማሳየት ቀላል እንዳልሆነ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከፍተኛ ፍሬ ያስገኛል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ዛሬ አጠናቀዋል።
አይ.ኤም ኤፍ እስከ አኹን ወደ1.5 ቢሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ መልቀቁን ኃላፊዋ ገለጹ
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ በጀመረችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የመጀመሪያዎቹ ወራት በታየው ስኬት ምክኒያት እስከ አኹን 1.5 ቢሊዮን ዶላር መለቀቁን የተናገሩት፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም /አይ.ኤም.ኤፍ/ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ፣ ዜጎቿ ውጤቱን በትዕግሥት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።