"የሰሜኑ እርምጃ የሚጠናቀቀው ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው"- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

  • እስክንድር ፍሬው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

በህወሓት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረብ በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

"ኢትዮጵያ ሁኔታው እንደሚያሳስባቸው የገለፁ ወዳጆቿን ታመስግናለች" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግን የአንዲት ሉዓላዊት ሃገር የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሌላም በኩል “የኢትዮጵያ አየር ሃይል የጦር ጄት መትተን ጥለናል” በሚል በህወሓት የተሰጠውን መረጃ የመከላከያ ሚኒስቴር አጣጥሏል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሀመድ ተሠማ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ መረጃው ሕዝብን ማደናገሪያ ነው በማለት ነው ያስረዱት።

“የተመታ ጄትም የለም። ጄቶቻችን በሥራ ላይ ናቸው” ብለዋል ጄነራሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

"የሰሜኑ እርምጃ የሚጠናቀቀው ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው"- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ