የሳውዲ አረቢያ የ90 ቀናት ቀነ ገደብ አንድ ቀን ብቻ ቀረው!
Your browser doesn’t support HTML5
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ የመጨረሻው ሳምንት ምን ይመስል ነበር? ከሪያድ ከተማ የምዝገባ ጣቢያ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ መሪ /ኃላፊ/ አቶ ሻውል ጌታሁንን አነጋግረን ነበር። ይህ መረጃ የተሰጠን ከቀናቶች በፊት ነው። 60ሺህ የነበረው የተመዝጋቢ ቁጥር በመጨረሻዎቹ ቀናት ከ80ሺህ በልጧል። ይኖራሉ ተብለው ከሚገመቱት 400 ሺህ ገደማ ከሚደርሱት ፈቃድ ከሌላቸው ኢትዮጵያውያን ጋር ሲነጻፀር አሁንም የተመዘገበው ተመላሽ ቁጥር አነስተኛ ነው። ለድምጽ ጥራቱ ይቅርታ እንጠይቃለን።