"ሻንጣችንን ተሸክመን ሜዳ ላይ ወድቀናል" ትኬት ቆርጠው መንገዳቸውን የሚጠባበቁ ተመላሾች
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች መንግስታት የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ እንዲራዘም ቢጠይቁም ከሳውዲ መንግስት የተሰጠ ምላሽ የለም። የኢ/ አየር መንገድ ከተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ሳምንታዊ የበረራ ቁጥሩን ለማሳደግ ጥረት ቢያደርግም በሳውዲ አቪየሽን ፈቃድ ያገኘው ለተጨማሪ 17 በረራዎች ብቻ መሆኑን ከድርጅቱ ተረድተናል። በርካታ ተመላሾች በአውሮፕላን ትኬትና በበረራ እጥረት ምክንያት እየተንገላቱ እንደሆነ ይናገራሉ።