በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ የተመራው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ሰሞኑን ዝርዝር የሥራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡
አዲስ አበባ —
በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ የተመራው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ሰሞኑን ዝርዝር የሥራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ አዋጁ ከተነሣ በኋላም የቀጠሉና በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ያሏቸውን አንዳንድ ግጭቶች በዘላቂነት ለመፍታት የፌደራልና የክልል የፀጥታ መዋቅሮች ተቀናጅተው እየሠሩ ናቸው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሣ አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈው ሣምንት ከመንግሥት ጋር የተወያዩት ተቃዋሚዎች ግን ምክር ቤቱ ሰለመኖሩ እንኳን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ለሀገሪቱ የሚበጀው ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ስለ ሃገሪቱ ፀጥታ