በሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን ያደረጉት ጉብኝት ካሳካቸው ጉዳዮች አንዱ ሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲን ለማስፈታት ጫፍ ላይ መደረሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉዟቸው እንደተመለሱ በሚሌንየም አዳራሽ በተካሄደ “የአስተሳሰብ መገንቢያና ማነቃቂያ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ለሳዑዲ አረቢያ አልጋወራሽ አሥር ጥያቄዎችን አቅርበዋ ዘጠኙ ወዲያው መልስ ማግኘታቸውን አመልክተዋል።
በሳዑዲ አረቢያ እሥር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ማስለቀቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀው ሼህ አል-አልአሙዲንም ቢሆን እንደሚፈቱላቸው አልጋወራሹ ሌሊት ላይ ቃል ገብተውላቸው እንደነበረና ይሁን እንጂ ከቤተባቸው አባላት በደረሰባቸው የበረታ ጫና ምክንያት ሃሣባቸውን መቀየራቸውንና ለጊዜው ባሰቡት መሠረት ይዘዋቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናግረዋል።
“የትም ቢሆን የአንድ ኢትዮጵያዊ መታሠር ሁሉም ቦታ የሁላችንም መታሠር ነውና በተለይ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አል-አሙዲ እንዲፈቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ እጠይቃለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አል-አሙዲ ‘በቅርብ ይፈታሉ’ የሚል ብርቱ ተስፋ እንዳላቸው አብይ አሕመድ አስታወቁ