አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ መሠረት የሚይዝበት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ —
አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ መሠረት የሚይዝበት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
የ2011 ዓ.ም. ቅድሚያ ተግባሮቻቸውም ተቋማትን ማጠናከርና አዳዲሶችንም መፍጠር እንደሚሆን ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያዊያን አዲሱን ዓመት በሰላም፣ በፍቅር፣ በመስጠትና በማገዝ እንዲቀበሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር አብይ አሕመድ “እያስመዘገቡ ናቸው” ያለችውን ለውጥ ያደነቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያንም የዕውቅና ሽልማት አበርክታላቸዋለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ጠ/ሚ አብይ የኢትዮጵያዊያን አዲስ ዓመት አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ