ኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶችን በመጣስ፣ ሰዎችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ማሰቃየትና ስብዕናን በሚያዋርድ ሁኔታ በመያዝ በዓለምአቀፍ ተቋማትና በሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎች፣ እንዲሁም በመደበኛ ዜጎቿ ስትወቀስ ቆይታለች።
ነገር ግን በቅርቡ መንግሥት እራሱ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይህንኑ የሀገሪቱን የመብቶች ጥሰት ታሪኮች እያረጋገጡ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእነዚያ ያለፉ ዓመታት የጭካኔና የሥቃይ አድራጎቶች በአደባባይ ይቅርታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል። የመንግሥት የሽብር አድራጎትም ብለው ጠርተውታል።
በተጨማሪም ከእስር እየተለቀቁ የሚገኙት እስረኞች ከእነ ጎደለና የተጎዳ አካላቸው ከእስር ቤት እየወጡ በሀገሪቱ ብሔራዊና የክልል ቴሌቭዥን ጭምር ቀርበው እየተናገሩ ነው።
እስረኞችን ስታነጋግር የቆየችው ጽዮን ግርማ - “ከእስር የተለቀቁት ሰዎች መልሰው እንቋቋሙ ምን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል? ድጋፉንስ ሊሰጣቸው የሚገባው ማነው?” የሚሉና ሌሎች ጭያቄዎችን አንስታ የሕግ ባለሞያና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ተመራማሪ አካታ ተከታዩን ዘግባለች።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
ከእስር የተፈቱ ሰዎች ቀጣይ ሕይወት