በሳውዲ አረቢያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲና ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩን እያጣራ ነው
ዋሽንግተን ዲሲ —
መስከረም 13 ቀን በሀጂ ጸሎት ላይ ሳሉ በድረሰ መገፋፋትና መጨናነቅ በደረሰው አደጋ ከሞቱት 769 ሰዎች መካከል 13 ኢትዮጵያዊያን እንዳሉበት የገለጹት ሀጂ መሀመድ አሚን የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ናቸው።
“ከዚህ በፊት የሞቱትን ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 13 መሆኑ ታውቋል” ብለዋል በቪዲዮ ባስረጩት መልእክት።
Your browser doesn’t support HTML5
ሙሉ የድምጽ ዘገባውን ያዳምጡ
ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ የውጭ ሀገር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አስተባባሪ ኢማም ሼህ ሳልሃዲን ወዚር አብዛኞቹ ሟቾች በእስልምና ሃይማኖት አስተምሮትና እምነት መሰረት መካ ላይ የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈጽሟል።