በእሥራኤል የጋዛ ሠርጥ ወሰን ላይ ዛሬ በተነሣ ግጭት ቢያንስ አንድ ፍልስጥዔማዊ ተገድሎ ሌሎች ቁጥራቸው አርባ የሆነ ሰዎች ቆስለዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአንድ ሣምንት በፊት በዚያው አካባቢ ተካሂዶ በነበረ ሁከት የበረታበት የተቃውሞ እንቅስቃሴ 19 ፍልስጥዔማዊያን በእሥራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በሺሆች የሚቆጠሩ ፍልስጥዔማዊያን ወደ ጋዛ ወሰን አካባቢ መጉረፋቸውና እዚያ ሲደርሱም የእሥራኤል ወታደሮች ከኃይል ጋር እንደተቀበሏቸው ተዘግቧል።
ሰልፈኞቹ የድንበሩን አጥር እንዳይጥሱ ለማቆም በሚል ወታደሮቹ አስለቃሽ ጋዝ፣ የጎማ ጥይቶችና በእውን የእርሣስ ጥይቶች ተኩስ ከፍተውባቸዋል።
የዛሬውንና መሰል ጥቃቶችን ‘ከመጠን ያለፈ ኃይል ነው’ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ኅብረትና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች አውግዘውታል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የጋዛ ድንበር ግጭት ዛሬም ቀጥሏል