"በየቀኑ 2 እንቁላል እበላለሁ በቃ ይኸው ነው" ኤማ ሞራኖ የአንድ መቶ አስራሰባት ዕድሜ ባለፀጋ

Your browser doesn’t support HTML5

ጣልያናዊቷን ኤማ ሞራኖ ን እናስተዋውቃችሁ። የአንድ መቶ አስራሰባት አመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው። በአስራዘጠነኛው ክፍለዘመን እ.አ.አ በህዳር 27 ቀን 1899 ዓ.ም ነበር የተወለዱት። የእኚህ አዛውንት እድሜ በአለማችን በአስራዘጠነኛው ክፍለዘመን ከተወለዱትና ረጅም እድሜ ከኖሩት ሁሉ ቀዳሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።