የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በደቡብ ሱዳንና በማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፐብሊክ ያለው አመፅ በሚቆምበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የአፍሪቃ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።
አዲስ አበባ —

የኬሪ የጉብኝት የመጀመሪያ ወደሆነችው ኢትዮጵያ ረቡዕ ምሽት የገቡ ሲሆን፣ አብሯቸው የሚጓዘው የቪኦኤ ጋዜጠኛ ስካት ስተርንስ እንደዘገበው ሚስተር ኬሪ ነገ ሐሙስ፣ የጉዟቸው ዋነኛ አጀንዳ በሆነው በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ላይ፣ አዲሳባ ውስጥ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያና ከዩጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ይመክራሉ።
ሚስተር ኬሪ ለደቡብ ሱዳን መንግሥትና ለሽምቅ ተጊዎቹም ከበድ ያለ መልዕክት እንዳላቸው አንድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ገልፀዋል።
ኬሪ በአዲሳባ ቆይታቸው የማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፐብሊክን ቀውስ አስመልክተው ከአፍሪቃ ሕብረት ባለሥልጣኖች ጋርም ይገናኛሉ።
የአል-ቃዒዳ ግብር አበር በሆነው አል-ሻባብ ላይ ስለሚካሄደው ጦርነትም ለመነጋገር ከሶማልያው ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር እንደሚገናኙም ተገልጿል።
ሚተርስሰበስተር ኬሪ አዲሳባ የገቡት፣ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችና ዓምደኞች በታሠሩ በቀናት ልዩነት ውስጥ መሆኑ ነው።
ይህን የጋዜጠኞች መታሠር ለኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ያነሱ እንደሆን በትዊተር ተጠይቀው ጉዳዩ ከፍተኛ መሆኑንና ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለፕሬስ ነፃነት ያላት አቋም የፀና መሆኑን በትዌተር መልሰዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዙትን የድምፅ ፋይልሎች ያዳምጡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ ለአቀባበላቸው ልምምድ ሲደረግ የእርሣቸውን ቦታ በሌሉበት ሲሸፍን ከነበረ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጋር ቁመታቸውን ሲያስተያዩ /ፎቶ - ፋይል፤ ዕሁድ - ግንቦት 18/2005 ዓ.ም/
Your browser doesn’t support HTML5
ኬሪ አዲስ አበባ ገቡ
Your browser doesn’t support HTML5
የደቡብ ሱዳን ድርድር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአፍሪካ ጉብኝት