ኬንያ ያሉ ስደተኞች ብሦት ቀጥሏል

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች የታሠሩበት የናይሮቢው ካሳራኒ ስታዲየም

ኬንያ በስደተኞች ላይ እያካሄደች ነው የሚባለው የአፈሣ እና የማሠር እርምጃ እስከትናንት ምሽት መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ኬንያ ያሉ ስደተኞች ብሦት ቀጥሏል


ኬንያ በስደተኞች ላይ እያካሄደች ነው የሚባለው የአፈሣ እና የማሠር እርምጃ እስከትናንት ምሽት መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

ትናንትናና ዛሬ ወደ 55 ኢትዮጵያዊያንና ከ86 እስከ 90 የሚሆኑ ሶማሊያዊያን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ስደተኞቸ አመልክተዋል፡፡

ለቪኦኤ ያሉበትን ሁኔታ የተናገሩ ሰዎች እርምጃው አግባብነት የሌለውና ሥርዓትን የጠበቀ አይደለም ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ “ሕገወጥ ፍልሰተኞች አሉ” በሚል ሰበብ ፖሊስ አፈሣውን ተገን አድርጎ ጉቦ እየተቀበለና እያንገላታታቸው መሆኑን እዚያ የሚገኙ የሶማሊያ ስደተኞች ለዘጋቢያችን ጌብ ጃሰሎ ነግረውታል፡፡

የኬንያ ፖሊስ ደግሞ ስለጉቦው ከጭምጭምታና ከሐሜት በስተቀር በይፋ የቀረበልኝ ክስ የለም ብሏል - ለቪኦኤ፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡