ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት የሎስ አንጀለስ ንግድ ቡድን አባላት
Your browser doesn’t support HTML5
የሎስ አንጀለስ ንግድ ልዑካን አዲሳባን ጎበኙ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረውን አዲስ በረራ ምክንያት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ የተጓዘው የሎስ አጀለስ የልኡካን ቡድን ከአዲስ አበባ የንግድ ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርሟል።
የሎስ አንጀለስ ከተማ የንግድ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ካርሎስ ቫል ዳራም ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባና በሎስአንጀለስ መካከል የተጀመረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ለማክበር ነው ብለዋል።
ቦይንግ 767 አይሮፕላን - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
አየር መንገዱ በሣምንት ሦስት ጊዜ ወደ የሎስ አንጀለስ ከተማ በረራ መጀመሩም ታላቅ የኢኮኖሚ ጥቅም እንደሚያስገኝ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ጋር ቡድናቸው የተፈራረመው የመግባቢያ ሠነድም ሁለቱም ተቋማት የሚወክሏቸውን አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች እንደ ድልድይ ሆኖ የማገናኘት ዓላማ እንዳለው ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል፡፡
Chamber of Commerce
ስምንት የሎስአንጀል ከተማ የንግድ ተቋማትን ተጠሪዎች ያቀፈው ቡድን ማክስኞ ማታ ምዕራባዊቱን የዩናይትድ ስቴትስ የሲኒማ ማዕከል ከተማ የማስተዋወቅ ዝግጅትም በሸራተን ሆቴል አካሂዷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ።