በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን በገንዘብ ትረዳላችሁ በሚል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ 56ቱም ተጠርጣሪዎች ከ10 ቀን ቆይታ በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል፡፡
ድሬዳዋ —
በሜታ ወረዳ ሥር በሚገኙት የቁሉቢና ጨለንቆ ከተሞች ባልታወቀ ሰዓትና ቦታ ተሰብስባችሁ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ን በገንዘብ ረድታችኋል በሚል ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ 8 የቁልቢ እና 48 የጨለንቆ ከተማ ነዋሪዎች ዋስትና ተፈቅዶላቸው ከእስር ተፈተዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በቁልቢና ጨለንቆ ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ ተለቀቁ