በመተሐራ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው መሬት መንቀጥቀጥ ነዋሪዎችን አሳስቧል

Your browser doesn’t support HTML5

በመተሐራ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው መሬት መንቀጥቀጥ ነዋሪዎችን አሳስቧል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን መተሐራ ከተማ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እንዳሰጋቸው ነዋሪዎች ገለጹ። ትላንት ማምሻውን የተከሰተውን መንቀጥቀጥ ተከትሎ የግንብ አጥሮች መሰንጠቃቸውን እና በፈንታሌ ተራራ ላይም ናዳ በመከሰቱ ከተማዋ በአቧራ ተሸፍና መዋሏን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል።