ባለፈው ሳምንት መጀመርያ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር ድርድር ሁለቱ ተደራዳሪዎች ከስምምነት ሳይደርሱ ተጠናቋል።
ናይሮቢ —
ባለፈው ሳምንት መጀመርያ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር ድርድር ሁለቱ ተደራዳሪዎች ከስምምነት ሳይደርሱ ተጠናቋል።
ONLF
የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ሜህሪ ድርድሩ ሥምምነት የመፈራረም ሳይሆን ለሌላ ድርድር የመዘጋጀት እንደሆነ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።
ድርድሩ በአዲስ መልክ በ2012 የተጀመረ ሲሆን የኬንያ መንግሥት በአደራዳሪነት ለ4ኛ ጊዜ ሁለቱን አደራድሯል።
ONLF
ከአደራዳሪዎቹ አንዱ የሆኑት የኬንያ ጋሪሳ ግዛት ገዢ አቶ ዓሊ ኮራኔ ከዚህ በፊቱ ድርድር የተሻለ እንደነበረ ገልፀዋል። ባለፈው ቅዳሜ ከሰዓትም ድርጅቱ ኬንያ ለሚገኙ ደጋፊዎች ከኢህአዴግ መንግሥት ጋር እያደረገ ስላለዉ ድርድር ማብራርያ አድርጓል።
ስለድርድሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እስካሁን የተናገረው ነገር የለም።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
"ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በ24 ዓመት ውስጥ 40 ድርድሮች አድርገናል"-የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር