በርካታ ዓመታትን ያስቆጠሩ የብሔራዊ ቤተመንግሥት ታሪካዊ ተሽከርካሪዎች

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

በርካታ ዓመታትን ያስቆጠሩ የብሔራዊ ቤተመንግሥት ታሪካዊ ተሽከርካሪዎች

በፈረንሳይ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውና በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ካካተታቸው ነገሮች አንዱ የተሽከርካሪዎች ትዕይንት ማሳያ ሰፍራ ነው።

ከቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ድረስ የነበሩ መሪዎች የተገለገሉባቸውና የተለያዩ አገራት አቻዎቻቸውን ያስተናገዱባቸው ተሽከርካሪዎች በስፍራው ለዕይታ መቅረባቸውን የብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየምና ቅርስ አስተዴደር ማዕከል ኃላፊ ምንተስኖት ጢቆ ይናገራሉ።

ለትዕይንት ከቀረቡት ተሽከርካሪዎች መካከል፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ መሪ የነበሩት ማርሻል ቲቶ እና የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ ወታደራዊ ትዕይንቶችን በአዲስ አበባ የተመለከቱባት በአሜሪካን የተመረተች ላንድ ሮቨር ተሽከርካሪ ትገኛለች።

ተሽከርካሪዋ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና በኮሎኔል መንግሰቱ ኃይለማርያም የስልጣን ዘመን አገልግሎት መስጠቷን አቶ ምንተስኖት ጠቅሰዋል።

ሌሎች ታሪካዊ ተሽከርካሪዎችና ንጉሳዊ የባቡር ፉርጎዎችም በዚህ የተሽከርካሪዎች ትዕይንት ማሳያ ስፍራ ይገኛሉ።